Fana: At a Speed of Life!

የመውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመውጫ ፈተና በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ለሚመረቁ ተማሪዎች በመጪው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም 200 ሺህ ከመንግሥትና ከግል ዩኒቨርሲቲ የሚመረቁ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል፡፡

በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ኤባ ሚጀና በጉዳዩ ዙሪያ በተዘጋጀ ዐውደጥናት ላይ እንደገለጹት÷ የመውጫ ፈተና በመጪው ሰኔ ወር ለሁሉም ቅድመ መደበኛ ተማሪዎች በአንድ ጊዜ ይሰጣል።

የመጀመሪያው ፈተና በሰኔ ወር ከተሰጠ በኋላ ቀጣዩ የመውጫ ፈተና ደግሞ ከሥድስት ወራት በኋላ ይሰጣል ማለታቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ዴስክ ኃላፊ ሰዒድ መሐመድ በበኩላቸው ፈተናው ለሁሉም ተማሪዎች በኦንላይን እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

ይህም የፈተና ስርቆትን ለመከላከል የተሻለ አማራጭ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

በዚህም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱና ተፈታኝ ተማሪዎች ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርጉ ተጠይቀዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.