Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከሶማሊያ ፖሊስ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስና የሶማሊያ ፖሊስ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ ድንበር ዘለል በሆኑ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት የሚያስችል ሲሆን÷ በተለይ ሽብርተኝነትንና ህገ-ወጥ የሰዎችንና ጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመከላከል በጋራ መስራት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ስምምነቱ የሶማሊያ ወጣት ፖሊስ አመራሮች በኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሌጅ ገብተው ስልጠና እንዲያገኙ የሚያደርግ መሆኑም ታውቋል፡፡

በዚህም በቅርቡ ከ40 በላይ የሚሆኑ የሶማሊያ ፖሊስ አባላት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ ስልጠና እንደሚወስዱ ተመላክቷል።

ስምምነቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ከሶማሊያ አቻቸው ሜጀር ጀነራል አብዲ ሀሰን መሀመድ ጋር መፈራረማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.