Fana: At a Speed of Life!

ቻይና እና ሳዑዲ ዓረቢያ በመከላከያ ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና እና ሳዑዲ ዓረቢያ በመከላከያ እና ኢነርጂ ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ተስማምተዋል፡፡

በሳዑዲ ዓረቢያ የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ÷ ከሀገሪቱ ንጉስ ሠልማን ቢን አብዱል አዚዝ አል ስዑድ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሀገራቱ የጋራ ጥቅማቸውን ባስጠበቀ መልኩ በተለያዩ ዘርፎች በቅንጅት ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ነው የተገለጸው፡፡

ሀገራቱ በዓለም አቀፉ የነዳጅ ዘይት ገበያ ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎት በድጋሚ ማረጋገጣቸውም ተመላክቷል፡፡

በተለይም ሀገራቱ በመከላከያ ዘርፍ እና በሃይል አቅርቦት ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር መፈራረማቸውን ሺንዋ ዘግቧል፡፡

ሀገራቱ ስትራቴጂያዊ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከርም የውስጥ ጉዳዮቻቸው ላይ ጣልቃ ያለመግባት መርህን አክብረው እንደሚንቀሳቀሱ አስታውቀዋል፡፡

የፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ የሳዑዲ ጉብኝት ሪያድ ከዋሽንግተን ጋር ያላት የሁለትዮሽ ግንኙነት እየተቀዛቀዘ በመጣበት ወቅት መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.