Fana: At a Speed of Life!

ሰዋሰው መልቲ ሚዲያ የሞባይል መተግበሪያ ከሙዚቃ ባለሙያዎች ጋር መሥራት የሚያስችለውን ሥምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሰዋሰው” መልቲ ሚዲያ የሞባይል መተግበሪያ ከሙዚቃ ባለሙያዎች ጋር መሥራት የሚያስችለውን ሥምምነት ተፈራርሟል፡፡

አንጋፋዋን ድምጻዊት ማሪቱ ለገሰን ጨምሮ ቴዎድሮስ ካሳሁን፣ ካሙዙ ካሳ፣ አብነት አጎናፍር፣ ግርማ ተፈራ፣ ሔኖክ አበበ፣ ራሄል ጌቱ፣ ያሙሉ ሞላ፣ ለምለም ኃ/ሚካኤል፣ ብሌን ዮሴፍ፣ ዘሩባቤል ሞላ እና ሌሎች ከ80 በላይ አንጋፋና ወጣት የሙዚቃ ባለሙያዎች ከ“ሰዋሰው” ጋር ለመስራት የስምምነት ሰነድ መፈረማቸው ተገልጿል፡፡

በስምምነት ስነ ስርዓቱ ላይ ደራሲያን፣ አቀናባሪዎች እና ፕሮዲውሰሮች መገኘታቸው ተመላክቷል፡፡

የፊርማ ሥነ-ሥርዓት እና የአልበም ምርቃትን ጨምሮ የክፍያ ሥርዓት (ፕሪምየም) ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ መካሄዱ ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ በተካሄደው መርሐ-ግብር የሙዚቃ አቀናባሪ የሆነው የካሙዙ ካሳ “ሻኩራ” የተሰኘ አልበም የተመረቀ ሲሆን÷ አልበሙ በሰዋሰው መልቲ ሚዲያ የሞባይል መተግበሪያ ላይ ተለቋል።

ሰዋሰው መልቲ ሚዲያ ሙዚቃን በቀላሉ በኦንላይን ለመገበያት የሚያስችል የመተግበሪያ ዘዴ ሲሆን÷ መልቲሚዲያ በዘርፉ ባሉ የጥበብ ባለሙያዎች ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱ ተጠቁሟል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.