Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን የልማት እና የቴክኒክ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በሰላም ስምምነቱ ትግበራ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጡ።
አቶ ደመቀ በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረውን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በመንግስትና በህወሓት መካከል በተደረገው ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ መስጠታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በሰላም ስምምነቱ መሰረት ሰብዓዊ እርዳታ በማቅረብና መሰረታዊ አገልግሎቶችን በማስጀመር ረገድ አበረታች ተግባራት መከናወናቸውንም አብራርተዋል።
በጦርነቱ የወደሙ ትምህርት ቤቶችንና ጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባት መንግስት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.