Fana: At a Speed of Life!

የማይጫው ከተማ እና አካባቢው ኤሌክትሪክ ሃይል ዳግም አገኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማይጫው ከተማ እና አካባቢው ኤሌክትሪክ ሃይል ዳግም ማግኘታቸውን በኢትጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

በአገልግሎቱ የወልድያ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሽመል ወ/ሰማያት÷በጦርነቱ ምክንት ኃይል ተቋርጦባቸው የነበሩ የማይጫው ከተማና አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ሃይል ዳግም ማግኘታቸውን ገልፀዋል፡፡

አካባቢው የኤሌክትሪክ ሃይል ዳግም ያገኘው ከአላማጣ-ማይጨው የተዘረጋው የ66 ኪሎ ቮልት የሃይል ማስተላለፊያ መሰመር ጥገና ተከናውኖ በመጠናቀቁ ነው ብለዋል፡፡

ዳይሬክተሩ በጥገና ሂደቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የተቋሙ ባለደረቦችና ድጋፍ ላደረጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በቀጣይ ሌሎች ኤሌክትሪክ የተቋረጠባቸው አካባቢዎች መልሰው እንዲያገኙ በትኩረት እንደሚሰራ መግለጻቸውንም በኢትጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.