Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የቀረቡለትን 10 አባላት ተቀብሎ አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ያለው የብልፅግና ፖርቲ አንደኛ ጠቅላላ አስቸኳይ ጉባኤ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ሆነው እንዲካተቱ የቀረቡለትን 10 አባላት ተቀብሎ አፀደቀ።

ጉባኤው በዛሬ ከሰዓት ውሎው በፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብርሃም አለኽኝ አቅራቢነት በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንዲካተቱ የተመረጡ አባላትን ተቀብሎ አፅድቋል።

በዚህም መሰረት የብልፅግና ፖርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ሆነው የተካተቱት ጁል ናንጋል ከጋምቤላ፣ ቀበሌ መንገሻ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች፣ መስከረም ደበበ ከኦሮሚያ፣ታደሰ ገብረ ፃዲቅ ፣ አብርሀም አያሌው፣ ዲያቆን ተስፋሁን ባንተያብል፣ ደሳለኝ ጣሰው፣ ወርቁ ሃይለማርያም፣ ዘውዱ ማለደ እና መሀመድ ያሲን ከአማራ ክልል ናቸው።

አቶ አብርሀም ለጉባኤው እንዳስረዱት÷ በማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እንዲካተቱ የተደረገው ምርጫ ቦርድ እንዲስተካከል ያስቀመጠውን አቅጣጫ ተከትሎ በፖርቲው መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 17 ንኡስ አንቀፅ ( ሸ) መሰረት የተከናወነ ነው።

ጉባኤው በተጨማሪም 11 የፖርቲውን ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን አባላትን ምርጫ እንደሚያካሂድም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.