Fana: At a Speed of Life!

አርጀንቲና ኔዘርላንድስን በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ አርጀንቲና እና ኔዘርላንድስ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡
በዚህም አርጀንቲና ኔዘርላንድስን በመለያ ምት 4 ለ 3 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀል ችላለች፡፡
ሁለቱ ቡድኖች መደበኛውን 90 ደቂቃ 2 ለ 2 በሆነ ውጤት ያጠናቀቁ ሲሆን÷በተጨማሪ ደቂቃውም ያለ ምንም ግብ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠ የመለያ ምትም አርጀንቲና 4 ለ 3 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.