Fana: At a Speed of Life!

የአሪ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ዲሽታ ጊና” በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኘው የአሪ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ “ዲሽታ ጊና” በዓል በጂንካ እየተከበረ ነው፡፡

በዞኑ የሚገኙ 16ቱም ብሔረሰቦች በተገኙበት እየተከበረ የሚገኘው “ዲሽታ ጊና”÷ ለአሪ ብሔረሰብ ከአሮጌ ወደ አዲስ ዘመን መሻገሪያ እና የአዲስ ነገር ጅማሬ መሆኑ ይታመናል፡፡

“ሎንጋ” በተባለው ወር መጀመሪያ የሚከበረው የብሔረሰቡ ዘመን መለወጫ በዓል “ዲሽታ ጊና” በጋራ የሚሰባሰቡበት እሴታቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአሮጌው ዓመት ከነበረው ድካምና ጥረት ወደ ጥጋብና እረፍት ማለፊያ የተትረፈረፈ ምርት ማግኛ የበረከት ተምሳሌት ተደርጎም ይወሰዳል፡፡

በዓሉ ሕዝቦች ለረጅም ዓመታት ተከባብረውና ተሳስበው እንዲኖሩ ያደረገ በመሆኑ÷ ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ መሥራት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

በመለሰ ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.