Fana: At a Speed of Life!

የፀጥታ ኃይሉ በተቀናጀ መልኩ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ትኩረት ሰጥቶ  እንደሚሠራ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፀጥታ ኃይሉ በተቀናጀ መልኩ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ ተገለጸ፡፡

ትኩረቱን በወቅታዊ ሀገራዊ የፀጥታ ጉዳይ ላይ ያደረገ የፌደራልና የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች አስቸኳይ የጋራ ስብሰባ በፉደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ተካሂዷል፡፡

በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በሽብርተኞች፣ በጽንፈኞች እና የተጀመረውን የፀረ-ሌብነት ትግል ለማደናቀፍና ሀገሪቷን ወደ ቀውስ ለመምራት አንዳንድ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም የመብት ጥያቄዎችን ሽፋን በማድረግ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን በማነሳሳት ሁከት ለመፍጠር በህቡዕ እየተንቀሳቀሱ መሆኑ በስብሰባው ላይ  ተገልጿል፡፡

በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ይህንን እንደ ሽፋን በመጠቀም ወደ ጥፋት መንገድ እያመሩ እንደሆነ በቀረበው መረጃ ተረጋግጧል መባሉን የፌደራል ፖሊሰ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.