Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ሀሰተኛ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር እና 95 ሺህ ዶላር ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ ሀሰተኛ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር እና 95 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መያዙ ተገለፀ፡፡

የጎንደር ከተማ አሰተዳደር ፓሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ዋና ሀላፊ ኢንስፔክተር እየሩሳሌም አስማረ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት÷ ሀሰተኛ ገንዘቡ እና ዶላሩ የተያዘው ዛሬ ከቀኑ 5 ሰዓት በከተማው ቀበሌ 18 ልዩ ቦታው ኮሌጅ አካባቢ በባለሶስት እግር ተሽከርካሪ ተጭኖ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር ነው ፡፡

በዚህም ሀሰተኛ ባለሁለት መቶ ብር ኖት 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር እና ሀሰተኛ 95 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በህብረተሰቡና በፀጥታ ሀይሎች ክትትል መያዝ ተችሏል፡፡

ሀላፊዋ አሽከርካሪውን ጨምሮ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው ማህበረሰቡ መሰል ወንጀሎችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

በሰላም አስመላሽ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.