Fana: At a Speed of Life!

ከ103 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የጉምሩክ ኮሚሽን ከኅዳር 23 እስከ 29 ቀን 2015 ባደረገው ክትትል ከ103 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ዕቃዎቹን የያዘው በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽኅፈት ቤቶች መሆኑንም በገፁ ባወጣው መረጃ አመልክቷል፡፡

ከተለያዩ ቅርንጫፍ ፅኅፈት ቤቶቹ 93 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የገቢ ኮንትሮባንድ ዕቃዎችን እና 9 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የገቢ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በድምሩ ከ103 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ነው መያዙን ያስታወቀው፡፡

አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሐኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ ዕቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ ዕጾች፣የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል፡፡

የገቢ ኮንትሮባንድ በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ሥፍራ የሚይዙት ሞያሌ፣ ኮምቦልቻ እና ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽኅፈት ቤቶች ሲሆኑ እቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና በኅብረተሰቡ ተሳትፎ በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ ነው የተያዙት፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን ሲያዘዋዉሩ የተገኙ 26 ግለሰቦችም በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ነው የተነገረው፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.