Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር እና የኢፌዲሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የሥራ ኃላፊዎች ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እና የኢፌዲሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የሥራ ኃላፊዎች ተወያይተዋል።

ሁለቱ ተቋማት የዓለም አቀፍና የሀገር አቀፍ የቀይ መስቀል መርኅዎችን መሠረት በማድረግ አብሮ ለመሥራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፍሬያማ ዉይይት ማካሄዳቸው ተመልክቷል፡፡

በማኅበሩ የቦርድ አመራር እና አባል ዶክተር ሰይፉ ጌታሁን የተመራው የሥራ ኃላፊዎች ውይይት ÷ በቀይ መስቀል አርማ አጠቃቀም ላይ እንዲሁም በሠላም እና በግጭት ወቅት በሚደረጉ ሰብዓዊ ድጋፎች ላይ መክሯል፡፡

በምክክሩ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበሩን መርኅዎች መሠረት ባደረገ መልኩ በጥምረት መሥራት እንደሚያስፈልግ አቋም ተይዟል፡፡

ሌቴናል ጀነራል ጥጋቡ ይልማ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ወክለው ተቋማቸው ኢትዮጵያ የፈረመችውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች አንደሚያከብርና አንደሚያስከብር ገልጸዋል፡፡

በሰብዓዊነት ጉዳዮች ላይ ከአሁን ቀደም የነበረው ትብብር በበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን ዕምነትም ተናግረዋል።

በቀጣይም የማኅበሩን መርሆኅዎች መሠረት ባደረገ መልኩ አብሮ ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ተዘጋጅቶ ተቋማዊ ግንኙነት እንዲፈጠር ሁለቱም ተቋማት መስማማታቸውን ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.