Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዘላቂ የልማት ግቦች ላይ የሚሠራ የልኅቀት ማዕከል ሊያቋቁም ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦች እንዲሳኩ በጥናትና ምርምር የሚደግፍ የልኅቀት ማዕከል ለማቋቋም እንቅስቃሴ መጀመሩን ገለጸ።

ማዕከሉ በዘላቂ ልማት ግቦች አስተዳደር ላይ ትኩረት ያደረገው ፕሮጀክት አካል እንደሆነም አመልክቷል።

ፕሮጀክቱን የኖርዌይ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ የሚደገፍ ሲሆን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የኦስሎና ማላዊ ዩኒቨርስቲዎች በጋራ የሚተገብሩት እንደሆነ ተገልጿል።

በጥናትና ምርምር፣አጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠና በመስጠት በኢትዮጵያ የሚከናወኑ የዘላቂ የልማት ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ መደገፍን እንደሚያካትት ተነግሯል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፕሮጀክቱ ዙሪያ የተለያዩ ቋሚ ኮሚቴዎችን ከወከሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር የተወያየ ሲሆን÷ በውይይቱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶክተር አክሊሉ አምሳሉ ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያን የዘላቂ ልማት ግቦች ለማሳካት የሚያግዝ ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዘላቂ ልማት ግቦች እንዲሳኩ የሚደግፍ የልህቀት ማዕከል ለማቋቋም እንቅስቃሴ መጀመሩን ጠቅሰው የልህቀት ማዕከሉ በሦስተኛና ሁለተኛ ዲግሪ ሰልጣኞችን ተቀብሎ እንደሚያሰለጥን ነው ያብራሩት።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ፣መስኖና ቆላማ አካባቢ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር አወቀ አምዛዬ÷ ፕሮጀክቱ ቅንጅታዊ አሰራሮች እንዲኖሩ የሚያግዝ መሆኑን አንስተው ኮሚቴው ፕሮጀክቱ ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.