Fana: At a Speed of Life!

ፈረንሳይ እንግሊዝን 2 ለ 1 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳይ እንግሊዝን 2 ለ 1 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቀለች።

በኳታር የዓለም ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ፈረንሳይ እና እንግሊዝ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡

በጨዋታው ፈረንሳይ 2 ለ 1 በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍጻሜ አልፋለች።

እንግሊዝ ካገኘቻቸው ሁለት ፍፁም ቅጣት ምቶች ውስጥ መጠቀም የቻለችው አንዱን ብቻ ነው።

ቀደም ብሎ በተካሄደ ጨዋታ ሞሮኮ ፖርቹጋልን 1 ለ 0 በማሸነፍ በአለም ዋንጫ ታሪክ ግማሽ ፍፃሜውን የተቀላቀለች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር ሆናለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.