Fana: At a Speed of Life!

የቤሕነን ታጣቂ ቡድን በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ተመለሰ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ሕዝብ ነጻነት ንቅናቄ (ቤሕነን) ታጣቂ ቡድን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት ጋር የሰላም ስምምነት በመፈራረም የሰላም እና የልማት ሥራዎችን በጋራ ለመሥራት ዛሬ ወደ ክልሉ ገብቷል።

ታጣቂ ቡድኑ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት በሱዳን ካርቱም በደረሱት የሰላም ስምምነት መሠረት ነው ቡድኑ የሰላም አማራጮችን በመከተል ወደ ክልሉ የተመለሰው፡፡

በስምምነቱ መሰረት የቡድኑ አባላት ትጥቃቸውን ፈትተው ተሃድሶ በመውሰድ በክልሉ የሰላም እና የልማት ሥራዎች ላይ እንደሚሰማሩ መገለጹን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

የቡድኑ አባላት ከሱዳን ድንበር ሸርቆሌ ወረዳ ገንገን ቀበሌ ጀምሮ ወደ ክልሉ ሲገቡ በአሶሳ ዞን የሸርቆሌ፣ የመንጌ የሆሞሻ፣ የዑራ፣ የአሶሳ እና የባምባሲ ወረዳ ነዋሪዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

የሰላም አማራጭን ተቀብሎ ወደ ክልሉ ለገባው የቤሕነን አመራሮች እና አባላት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ ማምሻውን አቀባበል እንደሚያደርጉላቸው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀሩን ዑመር ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.