Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪን ለመገደብ የወጣው ደንብ ለሦስት ወራት ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪን እና ተከራዮችን ማስወጣትን ለመገደብ የወጣው ደንብ ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት እንዲራዘም የክልሉ ካቢኔ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

የሐረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) የዜጎችን ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዚህ በፊት የመኖሪያ ቤት ተከራዮችን ማስለቀቅ እና የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሪን ለመገደብ ደንብ ማውጣቱ ይታወሳል።

በመሆኑም ዜጎችን ከተለያዩ ጫናዎች ለመከላከል ሲባል ይህ ደንብ ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት እንዲራዘም የክልሉ ካቢኔ ውሳኔ ማሳለፉን የሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚሁ መሰረት በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ተከራዮችን ማስለቀቅና እና የቤት ኪራይ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የተከለከለ መሆኑን የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.