Fana: At a Speed of Life!

12ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 12ኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በድሬደዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ዛሬ ይካሄዳል፡፡

በዚህ መሰረትም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ መቻል ከወልቂጤ ከተማ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን÷ ሀዲያ ሆሳዕና
ከአዳማ ከተማ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ፡፡

ፕሪሚየር ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ በ22 ነጥብ ሲመራ ኢትዮጵያ መድን በግብ ክፍያ ተበልጦ በተመሳሳይ 22 ነጥብ ሁለተኛ በመሆን ይከተላል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊሱ ኢስማኤል ኦሮ- አጉሮ በ11 ጎል በከፍተኛ ጎል አግቢነት ሲመራ÷ የወልቂጤ ከተማው ጌታነህ ከበደ
በ10 ጎል ይከተላል፡፡

የፋሲል ከነማው ፍቃዱ አለሙ እና የድሬዳዋ ከተማ ቢኒያም ጌታቸው 7 ጎሎችን በማስቆጠር 3ኛ እና 4ኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

መርሐ ግብሩ ቀጥሎ÷ ማክሰኞ ቀን 10 ሰዓት ድሬዳዋ ከተማ ከወላይታ ዲቻ፣ ምሽት 1 ሰዓት ሲዳማ ቡና ከ ባህርዳር ከተማ ጫዋታቸውን እንደሚያደርጉ ከሊግ ኩባንያው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.