Fana: At a Speed of Life!

ተመድ ለድንገተኛ እና ተገማች አደጋዎች ምላሽ ለመሥጠት እስካሁን 409 ሚሊየን ዶላር መሰብሰቡን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማዕከላዊ የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ፈንድ በ2023 ድንገተኛ እና ተገማች አደጋዎች ሲያጋጥሙ ተጋላጭ ሀገራትን በዕርዳታ ለመድረስ እስካሁን 409 ሚሊየን ዶላር መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

“ድጋፍ ለሁሉም ከሁሉም” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር ላይ ኢትዮጵያ ሥኬታማ ተሳትፎ እንደነበራት ተገልጿል፡፡

መርሐ-ግብሩ በአሜሪካ ኒውዮርክ የተካሄደ ሲሆን÷ የኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ስራ አመራር ኮሚሽንም ተሳታፊ ነበር፡፡

ኮሚሽኑ ÷ በሰሜኑ የሀገሪቷ ክፍል በተከሰተው ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ላጋጠሙ አደጋዎች ምላሽ ለመስጠት እና ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ የተከናወኑ ተግባራትን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በማስረዳት ረገድ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ስብሰባዎች ማካሄዱን ጠቁሟል።

ተመድ በፈረንጆቹ 2023 ድንገተኛ እና ተገማች አደጋዎች ሲያጋጥሙ አደጋዎቹ የተከሰተባቸውን ሀገራት በዕርዳታ ለመድረስ እና ለመደገፍ 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ለመሰብሰብ ዐቅዶ እየሠራ ነው ተብሏል፡፡

የመንግስታቱ ድርጅት የታቀደው ገንዘብ እስኪገኝ ጥረቱ አጠናክሮ እንደሚቀጥልማስታወቁንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.