Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 162 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 162 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመላሾቹ ውስጥም 1 ሺህ 154 ወንዶች እና 8 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ከህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ 10 ሺህ 820 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.