Fana: At a Speed of Life!

የሞሮኮ አየር መንገድ በ30 ልዩ በረራዎች ደጋፊዎችን ወደ ዶሃ ሊያመላልስ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሳሥ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሞሮኮ አየር መንገድ  የብሄራዊ ቡድን ደጋፊዎችን  ለማጓጓዝ ከካዛብላንካ ወደ ዶሃ 30 በረራዎች እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡

ኤር ማሮክ የተባለው የሞሮኮ አየር መንገድ በዛሬው እለት እንዳስታወቀውም ከካዛብላንካ ወደ ዶሃ የሚደረጉ 30 በረራዎች ማክስኞ እና ረቡዕ ይደረጋሉ ብሏል፡፡

አየር መንገዱ ይህን ያደረገው  ሞሮኮዊያን ዜጎችን ለማሰደስት እና ሀገሪቱ አፍሪካን ወክላ  በአለም ዋንጫው ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀሏን ተከትሎ ስለመሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

ሞሮኮ ፖርቹጋልን 1 ለ 0 በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን የተቀላቀለች ብቸኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ስትሆን በመጪው ረቡዕ ፈረንሳይን እንደምትገጥም ሲጂቲኤን በዘገባው ጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.