Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄን አስመልክቶ ላሳዩት አመራር “የአፍሪካ የላቀ አመራር” ሽልማት ተበረከተላቸው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄን አስመልክቶ ላሳዩት አመራር “የአፍሪካ የላቀ አመራር” ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄን አስመልክቶ ላሳዩት አመራር ‘የአፍሪካ የላቀ አመራር’ ሽልማት የተበረከተላቸው÷ “አፍሪካ የዓለም አቀፍ ንቅናቄ አጣዳፊነት” በሚል መሪ ሐሳብ አሜሪካን አካዳሚ ኦፍ አቺቭመንት እና ግሎባል ሆፕ ኮአሊሽን የተሰኙ ተቋማት በዋሽንግተን ዲሲ በጋራ ባዘጋጁት ልዩ ዝግጅት ላይ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም. የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን ስታስጀምር፣ በአራት ዓመታት ውስጥ 20 ቢልየን ችግኞችን ለመትከል ማቀዷ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያ ከታቀደው ግብ አልፋ በመላ ሀገሪቱ 25 ቢልየን ችግኞች በመትከል የአራት ዓመት ዕቅዷን አሳክታለች።

በዚህም የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ እና ለደን መልሶ ልማት ላደረገችው አስተዋጽዖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና አግኝታለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.