Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 7 አባላት ያሉት የጸረ-ሙስና ኮሚቴ ተቋቋመ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ሰባት አባላት ያሉት የጸረ-ሙስና ኮሚቴ አቋቋሙ።

ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ትግል በተደራጀ መልኩ ውጤታማ ለማድረግ ሰባት አባላት ያሉት የጸረ-ሙስና ኮሚቴ መቋቋሙን አቶ አሻድሊ ገልጸዋል፡፡

የጸረ-ሙስና ኮሚቴው ከዛሬ ጀምሮ ወደሥራ ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የክልሉ መንግስት ሙስናና ብልሹ አሠራርን በመከላከል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎችን ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል፡፡

የጸረ-ሙስና ትግሉ የሁሉንም የተቀናጀ ተሳትፎ  ስለሚፈልግ ለውጤታማነቱ የክልሉ ሕዝብ ጥቆማ ከመስጠት ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ እዲያደርግ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ጥሪ አቅርበዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.