Fana: At a Speed of Life!

ወጋገን እና አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንኮች በትግራይ ክልል ዳግም አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ወጋገን እና አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንኮች በትግራይ ክልል ዳግም አገልግሎት ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡

ተቋርጦ የቆየው የባንክ አገልግሎት እንዲጀመር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሰጠው ማሳሰቢያ መሰረት አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በትግራይ ክልል የባንክ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል፡፡

ባንኩ በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየውን አገልግሎት ለማስጀመር ኮሚቴዎችን አቋቁሞ የቅድመ ዝግጅት ሥራ መሥራቱን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መረጃ ገልጿል፡፡

በዚህም በጦርነቱ ወቅት በባንኩ ንብረትና ገንዘብ ላይ የደረሰ ጉዳት መጠን ለማጣራት የደንበኞች ሒሳብ ለማመሳካር፣ በክልሉ የሚገኙ ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት ካቋረጡበት ጊዜ ጀምሮ የነበረውን ክፍተት ከባንኩ ኮር ባንኪንግ ጋር አዋኅዶ ለማናበብና ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን በፍጥነት ለመሥራት የቅድመ ዝግጅት ሥራ መከናወኑ ተመላክቷል፡፡

በተመሳሳይ ወጋገን ባንክ በትግራይ ክልል በቅርቡ ሙሉ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.