Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 5 አባላት ያሉት የፀረ-ሙስና ኮሚቴ ተቋቋመ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በክልሉ ሌብነትን እና ብልሹ አሠራርን መታገል የሚያስችል 5 አባላት ያሉት የፀረ-ሙስና ኮሚቴ አቋቁመዋል።

የመንግስትና የህዝብን ሃብት ከብክነት ለመታደግ እንዲቻል ከመደበኛ የፀረ ሙስና ትግል ባሻገር ኮሚቴ አቋቁሞ መስራት ተገቢነቱ ታምኖበታል ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ።

በክልሉ ሙስና ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የተደራጀ ትግል ይጠይቃል ያሉ ሲሆን ÷ለዚህም በክልሉ ሌብነትን እና ብልሹ አሠራርን መታገል የሚያስችል 5 አባላት ያሉት የፀረ-ሙስና ኮሚቴ መቋቋሙን ገልፀዋል፡፡

ከአድሎ የፀዳ ተአማኒ መረጃና ጥቆማ ለትግሉ መሳካት ድርሻው የጎላ በመሆኑም በየደረጃው ያሉ የመንግስት አካላትና ህዝቡ ትግሉን እንዲደግፍ ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ጠይቀዋል።

የኮሚቴው አባላት ሥራቸውን በላቀ ቁርጠኝነትና በውጤታማነት እንዲያከናውኑም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.