Fana: At a Speed of Life!

ስደተኞች የሚያደርሱትን ተጽዕኖ ለመቀነስ ባለፉት 5 ዓመታት በተከናወኑ ተግራት ውጤት መመዝገቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ስደተኞች ተጠልለው በሚኖሩባቸው አካባቢዎች በሚገኙ ማህበረሰቦች ላይ የሚደርሰውን ተፅዕኖ ለመቀነስ ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ እንደነበሩ ተገለፀ።

11ኛው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) የስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክት የግምገማ መድረክ በጋምቤላ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የኢጋድ ተወካይና የስደተኞች ተጽዕኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ መሐመድ ኤልዱማ÷ በምስራቅ አፍሪካ ስደተኛ ተቀብለው የሚያስጠልሉ ሀገራት ስደተኞቹ የሚያደርሱትን ተጽዕኖ ለመቋቋም ፕሮጀክቱ ባለፉት አምስት ዓመታት ባከናወናቸው የልማት ሥራዎች የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ÷ ፕሮጀክቱ በክልሉ በሚገኙ አራት ስደተኛ ተቀባይ ወረዳዎች ያሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ሥራዎች ማከናወኑን ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በቀጣይ በሚኖረው ቆይታ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ማለታቸውን የጋምቤላ ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የስደተኞች ተጽዕኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክት የኢትዮጵያ ብሔራዊ አስተባባሪ ንጋቱ ቦጋለ ፕሮግራሙ÷ በጋምቤላ፣ አፋር፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ሶማሌና ትግራይ ክልሎች ስደተኞች በሚገኙባቸው 16 ወረዳዎች 117 ቀበሌዎች በርካታ የልማት ሥራዎችን አከናውኗል ብለዋል፡፡

በዚህም ትምህርት ቤቶችን፣ የሰው እና የእንስሳት ጤና ኬላዎችን፣ የንጹህ መጠጥ ውኃ ተቋማት፣ መንገዶች፣ አነስተኛ የገበያ ማዕከላት እንዲሁም አነስተኛ መስኖዎች መገንባታቸውንም ጠቁመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.