Fana: At a Speed of Life!

ለሀገራዊ የምክክር መድረክ መሳካት አመራሩ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ይኖርበታል- አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “ለአካታች ሀገራዊ የምክክር መድረክ መሳካት ሁሉም የብልፅግና ፓርቲ አመራር የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት ይኖርበታል” ሲሉ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

̎አቅምን በውጤት ፈተናን በስኬት̎” በሚል መሪ ሐሳብ ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በሐዋሳ ከተማ ሲሰጥ የነበረው የከፍተኛ አመራሮች የስልጠና መድረክ ተጠናቋል።

ስልጠናው÷ ፓርቲው የጀመራቸው የሰላም፣ የዴሞክራሲ እና የልማት መንገዶችን አጠናክሮ ማስቀጠል የሚችል አቅም በአመራሩ ዘንድ የሚፈጥር መሆኑ ተገልጿል፡፡

አቶ አደም ፋራህ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ በሰጡት የሥራ አቅጣጫ÷ የፓርቲውን እቅዶች፣ ስትራቴጂዎች እና ፖሊሲዎች በሙሉ ቁመና ለመተግበር አመራሩ የውስጠ ዴሞክራሲ ባህሉን ሊያሳድግ እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

የሚያጋጥሙ ችግሮችን በኅብረ ብሔራዊ አንድነትና በወንድማማችነት መንፈስ በጋራ የአንዳችን ቁስል የአንዳችን ህመም እንደሆነ ተረድተን ልንጋፈጣቸው ይገባል ማለታቸውን የፓርቲው ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

አመራሩ አንደ ሀገር ለማከናወን የታቀደው አካታች ሀገራዊ የምክክር መድረክ ስኬታማ አንዲሆን የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.