Fana: At a Speed of Life!

በአፋር በጦርነቱ በተጎዱ አካባቢዎች ከ200 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ፕሮጀክቶችሊተገበሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በጦርነቱ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች ከ200 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የልማት ፕሮጀክቶች ሊተገበሩ መሆኑ ተገለጸ፡፡

አቶ አወል አርባ በክልሉ በጦርነቱ በተጎዱ ወረዳዎች ላይ የሚሠሩ የልማት ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ከወርልድ ቪዥኝ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይዋል፡፡

በዚህም በቀጣይ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የልማት ፕሮጀክቶች እንደሚተገበሩ መገለጹን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡

ለፕሮጀክቶቹ ስኬታማነት የክልሉ መንግስት አስፈላጊውንድጋፍ እንደሚያደርግ አቶ አወል አረጋግጠዋል፡፡

በውይይቱ ላይ÷ የአፋር ክል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባን ጨምሮ የወርልድ ቪዥ ኢትዮጵያ ናሽናል ዳይሬክተር ከርሜን ተራዚኮ እና የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.