Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከ24 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉ ከ24 ሺህ በላይ ዜጎች የሚውል ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

ድጋፉ የተለያዩ የቤት ቁሳቁስን ያካተተ መሆኑን ኮሚቴው ገልጿል።

የተደረገው ድጋፍ በራያ ቆቦ እና አላማጣ ከተሞች ተፈናቅለው ለነበሩ ዜጎች የሚውል ነው ተብሏል።

ኮሚቴው ከዚህ ቀደም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በግጭትና በተለያዩ ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት ለተፈናቀሉና ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.