Fana: At a Speed of Life!

የባንክ አገልግሎት በአፋጣኝ እንዲጀመርላቸው የአላማጣ እና ኮረም ከተሞች ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአላማጣ እና ኮረም ከተማ አስተዳደሮች የባንክ አገልግሎት በአፋጣኝ እንዲጀመርላቸው ጠየቁ፡፡

የአላማጣ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኃይሉ አበራ እንዲሁም የኮረም ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሰላም ደበሳይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ከባንኮች በስተቀር ተቋርጠው የነበሩ አገልግሎቶች ዳግም ወደ ሥራ ተመልሰዋል፡፡
የስራ ሃላፊዎቹ የተጀመረውን አገልግሎት የበለጠ ለማጠናከር የባንክ አገልግሎት አለመጀመሩ በሥራቸው ላይ እንቅፋ መፍጠሩን ጠቁመዋል።

ከዚህ አንጻርም የሚመለከተው አካል አገልግሎቱን በአፋጣኝ እንዲያስጀምርላቸው ጠይቀዋል፡፡

ወጋገን እና አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንኮች በትግራይ ክልል ዳግም አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸውን ቅድመ ዝግጅት እንዳጠናቀቁ መግለጻቸው ይታወሳል።

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.