Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ- ሱዳን የባቡር ሐዲድ ግንባታ የአዋጭነት ግምገማ በካርቱም ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ሱዳንን በባቡር ሐዲድ ለማገናኘት ሲካሄድ የቆየውን የአዋጪነት ጥናት የሚገመግም አውደ ጥናት ዛሬ በሱዳን ካርቱም ተጀምሯል።

የሁለቱ ሀገራት ባለሙያዎችና የአማካሪ ድርጅቱ ተወካዮች የተገኙበት መድረኩ÷ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የደረሰውን የአዋጪነት ጥናት ገምግሞ በማጽደቅ በቀጣይ ሊወሰዱ በሚገባቸው እርምጃዎች ላይ መምከርን ያለመ ነው፡፡

በሱዳን የኢትዮጵያ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በግምገማው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ለሁለቱ ወንድማማች ሕዝቦች ግንኙነት የባቡር ሐዲዱ ግንባታ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰውን የቅድመ ጥናት ገምግሞ በማጽደቅና ፋይናንስ በማፈላለግ ፕሮጀክቱን እውን ማድረግ ይገባል ማለታቸውን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

የሱዳን የባቡር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዋሊድ አሕመድ በበኩላቸው÷ የሁለቱን ሀገራት የወጪና ገቢ ምርቶች ልውውጥ ለማሳለጥ እና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙቱን ለማጠናከር በባቡር ሐዲድ ማገናኘት ጠቃሚ መሆኑን አንስተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.