Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ለሲዳማ ክልል የእግር ኳስ ስፖርት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ለሲዳማ ክልል የእግር ኳስ ስፖርት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፉን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ጽኅፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ ለሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ አስረክበዋል።

በርክክቡ ወቅት ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ለተደረገው ድጋፍ ምሥጋና አቅርበው የእግር ኳስ ቁሳቁሱ በእግር ኳሱ ላቅ ያለ ውጤት ላስመዘገቡ ታዳጊዎች ድጋፍ እንደሚውል መግለፃቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡

አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ በበኩላቸው÷ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በሐዋሳ በነበራቸው ቆይታ 60 የእግር ኳሶች እና ለታዳጊዎች የሚውል 50 የእግር ኳስ ሙሉ ትጥቅ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸውን በማስታወስ ድጋፉ መደረጉን ገልፀዋል።

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.