Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለአፍሪካ-አሜሪካ የመሪዎች ጉባኤ ዋሽንግተን ዲ ሲ ይገኛሉ።
ከጉባኤው በተጓዳኝ ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተናግረዋል።
በውይይቱ ላይም በኢትዮጵያ ለሰሜኑ ግጭት ሰላማዊ እልባት እንዲሰጥ አሜሪካ ላደረገችው ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።
ለበርካታ አስርት ዓመታት ኢትዮጵያ የአሜሪካ ቁልፍ አጋር ሀገር ሆና መቆየቷን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ይህን አጋርነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረናል ብለዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.