Fana: At a Speed of Life!

የስንዴ ልማት ዕቅዱን ለማሳካት ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አቶ አወል አርባ ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል የስንዴ እርሻ ለማልማት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ተናገሩ፡፡

የክልሉ መንግስት ለስንዴ እርሻ ልማት አገልግሎት የሚውል ዘር እና ማዳበሪያ ከማቅረብ ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ነው አቶ አወል የገለጹት፡፡

በበጀት ዓመቱ የስንዴ እርሻ ለማልማት በክልሉ የተያዘውን ዕቅድ ለመፈፀም ቅድመ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ ወደ ሥራ ተገብቷል ማለታቸውን የአፋር ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

በጎርፍ ምክንያት የተበላሹ መስኖዎችን እና የእርሻ መሬቶችን ማስተካከል መቻሉንም አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.