Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ ከምድር በታች እየተገነባ የሚገኘው የትራፊክ ማኔጅመንት ህንፃ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ከተማን ስማርት ሲቲ በማድረግ በኩል አይነተኛ ሚና ያለው ዘመናዊ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ፕሮጀክቱ መሰረታዊ የትራንስፖርት እንቅስቃሴን የሚያሳልጥ እና የትራፊክ ፍሰት ስርዓቱን የሚያዘምን መሆኑንም ነው ከንቲባዋ በፌስ ቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት የጠቀሱት፡፡

በተጨማሪም በመንገድ ደህንነት ፣በወንጀል እንቅስቃሴ፣ በእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች፣ የአምቡላንስ አገልግሎቱን ለማቀላጠፍና ለማዘመን አገልግሎቱን ከአንድ ማዕከል መስጠት የሚያስችል ከመሬት ወለል በታች የተገነባ ባለአራት ወለል የዘመኑን የእድገት ደረጃ የዋጀ ፕሮጀክት መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ለግንባታው እና ለቴክኖሎጂ ገጠማው በአጠቃላይ ወደ 2 ቢሊየን ብር ወጪ እንደሚደረግበት ጠቅሰው፥ የተጀመረውን አዲስ አበባን በሁሉም መስክ ስማርት ሲቲ የማድረጉ ሥራ አይነተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.