Fana: At a Speed of Life!

ሊዮኔል ሜሲ የፍጻሜው ጨዋታ የመጨረሻ የዓለም ዋንጫ ጨዋታው መሆኑን ተናገረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ እሁድ የሚደረገው የፍሜው ጨዋታ የመጨረሻ የዓአለም ዋንጫ ጨዋታው መሆኑን ተናገረ።

የቀድሞው የባርሴሎና ኮከብ ለሀገሩ አርጀንቲና 171 ጊዜ የተሰለፈ ሲሆን፥ 96 ጎሎችን አስቆጥሯል።

በዓለም ዋንጫው 11ኛ ጎሉን በማስቆጠር የቀድሞውን የአርጀንቲና ኮከብ ጋብርኤል ባቲስቱታን ክብረ ወሰን ማሻሻል የቻለው ሜሲ፥ እሁድ በሚደረገው የፍፃሜ ፍልሚያ 172ኛ ጨዋታውን ያደርጋል።

ሜሲ ለአርጀንቲናው ሚዲያ ዲያሪዮ ዴፖርቲቮ ኦሌ፥ “ይህን ማሳካት እና ሀገሬን ለፍፃሜ ማድረስ በመቻሌ ደስተኛ ነኝ ብሏል፡፡

“ነገር ግን ቀጣዩ የዓለም ዋንጫ ብዙ ዓመታትን ይፈጃል” ያለው ሊዮኔል ሜሲ፥ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎው በእሁዱ የፍፃሜ ጨዋታ እንደሚቋጭ አረጋግጧል፡፡

ሜሲ ደምቆ ባመሸበት የትናንት ምሽቱ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ አርጀንቲና ለፍፃሜ ማለፏን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ አርጀንቲናውያን ብሄራዊ ቡድኑን በመደገፍ አደባባይ መውጣታቸውን ሱፐር ስፖርት ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.