Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክርስቲላ ጆርጂዬቫ ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ከአይ ኤም ኤፍ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

ውይይቱ በኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ፣ በዕዳ ማቅለያ አስፈላጊነትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑንም ጠቁመዋል።

“ያለፉትን ስኬቶቻችንን ለማስጠበቅ እና የጀመርናቸውን ለውጦች የበለጠ ለማጎልበት ቁርጠኝነታችንን እገልጻለሁ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.