Fana: At a Speed of Life!

ንፁሃንን ገድለዋል የተባሉ ተከሳሾች በሞት እና ዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በንፁሃን ላይ የሰው መግደል ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ ተከሳሾች በሞት እና ዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወሰነ፡፡

ተከሳሾቹ በሰገን ዙሪያ ወረዳ ሰገን ከተማ በአንድ ምግብ ቤት ላይ ቦንብ በመወርወር የሰው ሕይወት እንዲያልፍ፣  ከባድና ቀላል የአካል ጉዳትን ጨምሮ የንብረት ውድመት ማድረሳቸው ተገልጿል፡፡

በዐቃቤ ሕግ አምስት የወንጀል ክሶች የቀረቡባቸው 1ኛ ተከሳሽ ሰለሞን ከበደ ኃብተሚካኤል፣ 2ኛ ተከሳሽ ኦላታ ጀግና እና 3ኛ ተከሳሽ ዳኜ ገቢኖ  ላይ አስተማሪ ያለውን ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚህም ሁለተኛና ሦስተኛ ተከሳሾች በሞት እንዲሁም አንደኛ ተከሳሽ ደግሞ በ24 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ማሳለፉን የኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.