Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዲ ኤስ ቲቪ የቀጥታ ስርጭት ሊመለስ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዲ ኤስ ቲቪ የቀጥታ ስርጭት ከ13ኛ ሳምንት ጀምሮ ወደ ስርጭት ይመለሳል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን የምስል መብት የገዛው ዲ ኤስ ቲቪ በዓለም ዋንጫ ምክንያት ከ8ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ሁለት ጨዋታዎች ጀምሮ ያለፉትን አራት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታን ስርጭት ሽፋን ሳይሰጥ ቆይቷል፡፡

ይሁን እንጂ የዓለም ዋንጫው እሁድ የሚጠናቀቅ መሆኑን ተከትሎ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ የቀጥታ ሽፋን ከ13ኛ ሳምንት ጀምሮ እንደሚመለስ ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡

የዲ ኤስ ቲቪ የቀረፃ እና ፕሮዳክሽን ባለሙያዎች ነገ ዓርብ ድሬዳዋ እንደሚገቡ የተገለፀ ሲሆን የዓለም ዋንጫው እሁድ ከተጠናቀቀ በኋላ ከሰኞ ጀምሮ የሚደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች በዲ ኤስ ቲቪ ወደ ተመልካች የሚደርሱ ይሆናል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.