Fana: At a Speed of Life!

የዘንድሮው ኦዳ አዋርድ ታኅሣሥ 18 ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው ኦዳ አዋርድ ለ6ኛ ጊዜ ታኅሣሥ 18 እንደሚካሄድ ተገለጸ።

ኦዳ አዋርድ የኦሮሚኛ ቋንቋ የጥበብ ስራዎችንና ባለሙያዎችን አወዳድሮ እውቅና የሚሰጥ ሲሆን፥ በዘንድሮው የኦዳ አዋርድ ሽልማት ላይ አስተባባሪዎቹ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸው በዚህ ዓመት በሶስት ዘርፎች ማለትም በሙዚቃ፣ በመጽሐፍት እና ፊልም ስራዎች ባለሙያዎችንና ስራዎችንና አወደድሮ ባለሙያዎችን ይሸልማል ብለዋል።

የዘንድሮው ኦዳ አዋርድን በአፋን ኦሮሞ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በሐረሪ ክልል ቋንቋዎች ስራዎችን የሰሩ የእድሜ ዘመን የጥበብ ባለሙያዎችን መሸለሙ ደግሞ ከዚህ በፊት ከነበረው ለየት ያደርገዋል ነው የተባለው፡፡

በሲሳይ ወርቁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.