Fana: At a Speed of Life!

ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚውል የ120 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ120 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ሼህ መሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ያደረጉት የገንዘብ ድጋፍ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚውል መሆኑም ታውቋል።

ድጋፉ ለህክምና የሚውሉ የእጅ ጓንቶች፣ የፊት ማስኮች፣ ልዩ የለይቶ ማከሚያ ማዕከል የመከላከያ ጋዎኖች እንዲሁም ለተለያዩ የህክምና እቃዎች ግዢ የሚውል መሆኑን የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የገንዘብ ድጋፉን የተቀበሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሼህ መሃመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.