Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በበጋ ስንዴ ምርት ከ10 ሚሊየን ኩንታል በላይ ለማምረት እየሰራሁ ነው አለ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 6 ፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጋ ስንዴ ምርት ከ10 ሚሊየን ኩንታል በላይ ለማምረት እየሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ ሀይለማሪያም ከፍያለው እንደተናገሩት በክልል ደረጃ ከ250 ሺህ በላይ መሬት በስንዴ ዘር በመሸፈን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ ነው።

በዚህም በሁሉም ዞን የዘር መሸፈን ተግባር እየተካሄደ መሆኑን የጠቆሙት ሃላፊው ሂደቱ በዚህ ወር መጨረሻ ላይ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል።

በመሆኑም ከሚገኘው ምርት ላይ ሁለት ሚሊየን የሚሆነው ለውጭ ገበያ እንደሚቀርብ ገልጸዋል።

ክልሉ በዛሬው ዕለት በደቡብ ወሎ ዞን የበጋ ስንዴ ምርት ዘር የመሸፈን ተግባር የጀመረ ሲሆን በዞኑ ከ1 ሺህ ሄክታር በላይ የበጋ ስንዴ ዘር ተሸፍኗል ተብሏል።

እስከ ታኅሣሥ መጨረሻም በዞኑ ከ42 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመዝራት 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ኩንታል ለማግኘት እየተሰራ መሆኑም ነው የተገለጸው።

በከድር መሀመድና በአንድነት ናሁሰናይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.