Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ምክር ቤት ከፍተኛ ልዑክ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ አቅንቷል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የተመራ 9 አባላት ያሉት ልዑክ ለሥራ ጉብኝት ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ አቅንቷል፡፡
 
ልዑኩ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ሊሰራቸው ባቀዳቸው ትላልቅ የልማት ስራዎች እና ፕሮጀክቶች እንዲሁም የሐጅ ጉዞ የአሠራር ሂደቶችን መሻሻል በሚችልባቸው ሁኔታ ላይ ከሳዑዲ ዓረቢያ የስራ ሃላፊዎች ጋር እንደሚመክሩ ይጠበቃል::
 
የልዑካን ቡድኑ በዛሬው ውሎው ከሳዑዲ ዓረቢያ እስልምና ጉዳይ ሚኒስትር ጋር መክሮ በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመስራት ማስማማቱ ተገልጿል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.