Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ሳዑዲ ፓሊሳዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፓሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በኢትዮጵያ ከሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ፋሃድ ኦባይዱላህ አል-ሁመይዳኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም የህገ ወጥ ሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር፣ ሽብርተኝነትን ለመከላከል እና የሁለቱን ሀገራት ፓሊሳዊ ግንኙነት አጠናክሮ ማስቀጥጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
 
አምባሳደር ፋሃድ ኦባይዱላህ ÷ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የምስራቅ አፍሪካ የፓሊስ አዛዦች ህብረት ሊቀመንበር ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
 
የኢትዮጵያ ፌደራል ፓሊስ የድንበር ቁጥጥር አደረጃጀትን በሎጂስቲክስና በአቅም ግንባታ ለመደገፍ እንዲሁም የምስራቅ አፍሪካ የፓሊስ አዛዦች ህብረትን ለማገዝ ቃል መግባታቸውንም የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.