Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዋሺንግተን ዲሲ ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ እየተካሄደ በሚገኘው የአሜሪካ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸው ተገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ÷ከዚህ በፊት ዳያስፖራውን ጨምሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያነሳቸው የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት መንግሥት ባለፉት አራት ዓመታት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የሕግ ሪፎርሞችን ማከናወኑን ተናግረዋል፡፡

አሁን እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ዳያስፖራውም እያደረገ ያለውን ሀገሩን የማገዝ ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥሪ ማቅረባቸውንም ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.