Fana: At a Speed of Life!

ዩዜን ቦልት የቢቢሲ ስፖርት የሕይወት ዘመን ስኬታማ ሰው ሽልማትን አሸንፈ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 7፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጃማይካዊው አትሌት ዩዜን ቦልት የቢ ቢ ሲ ስፖርት የሕይወት ዘመን ስኬታማ ሰው ሽልማትን አሸንፏል፡፡

ቦልት ከሽልማቱ በኋላ ለቢቢሲ ስፖርት በሰጠው አስተያየት “ጠንክረህ ከሰራህ የምትፈልገውን ነገር እንደምታገኝ  እኔ ኅያው ምስክር ነኝ” ሲል ተናግሯል።

አባቴ ያስተማረኝ አንድን ነገር ለማሳካት ጠንክሮ መሥራት እንደሚያስፈልግ ነው ያለው ቦልት አባቱ÷ ቤተሰቡን ለማስተዳደር የሚያደርገው ጥረት ሁሉ ለስኬቱ ምሳሌ መሆኑን ገልጿል፡፡

የስምንት ጊዜ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊው ዩዜን ቦልት በቤጂንግ 2008፣ በለንደን 2012 እና በሪዮ 2016 ኦሎምፒኮች ሻምፒየን መሆን ችሏል፡፡

የ36 ዓመቱ ቦልት በ2009 የበርሊን የዓለም ሻምፒዮና 100 ሜትር ርቀት በ9 ነጥብ 58 ሰከንድ በመጨረስ የዓለም ክብረወሰን ባለቤት ነው፡፡

የ19 ጊዜ የዓለም ሻምፒየኑ ቦልት በነሐሴ 2017 ራሱን ከሩጫ ማግለሉ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.