Fana: At a Speed of Life!

ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የአማራ ሕዝብ ሙዚየም ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 7፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል መንግሥት ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የአማራን ሕዝብ ሙዚየም ማስገንባት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ሙዚየሙ የአማራን ሕዝብ ቅርስ፣ ታሪክና ባሕሉን ለማስቀመጥ ከማገልገል ባለፈ አንዱ የቱሪዝም መዳረሻ እንደሚሆን ታምኖበታል፡፡

በአማራ ሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የሚገነባው ይህ ሙዚየም 1 ቢሊየን 186 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግበትም ነው የተነገረው።

ሙዚየሙ የሚገነባው በባሕር ዳር ከተማ ሲሆን÷ ሙዚየሙ በአጠቃላይ በ15 ሺህ 600 ካሬ ላይ የሚያርፍ ይሆናል።

በሙዚየሙ የግንባታ ማስጀመሪያ መርሀግብር ላይ ከፍተኛ የክልሉ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል ሲል የዘገበው አሚኮ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.