Fana: At a Speed of Life!

ፖርቹጋል አሰልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስን ከሃላፊነት አነሳች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖርቹጋል አሰልጣኝ ፈርናንዶ ሳንቶስን ከአሰልጣኝነት አሰናብታለች።

የ68 አመቱ አሰልጣኝ ፖርቹጋል በዓለም ዋንጫው በሞሮኮ 1ለ 0 ተሸንፋ ከሩብ ፍፃሜ መሰናበቷን ተከትሎ ነው ከሃላፊነት የተነሱት።

የፖርቹጋል እግር ኳስ ማህበር ፈርናንዶ ሳንቶስ እና የቴክኒክ ቡድናቸው በስምንት አመታት ቆይታቸው ለብሄራዊ ቡድኑ ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

የፖርቹጋል እግር ኳስ ማህበር ቦርድ ቀጣዩን የብሔራዊ  ቡድን አሰልጣኝ የመምረጥ ሂደቱን በቅርቡ ይጀምራል መባሉን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል፡፡

ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር ስምንት አመታትን ያሳለፉት ሳንቶስ በ2016 የአውሮፓ ዋንጫ ቡድኑን በምመራት ሻምፒዮን ማድረግ ችለዋል።

ከዚህ ባለፈም በአዲሱ የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ በ2018/19 ቡድኑን አሸናፊ አድርገውታል።

አሰልጣኙ በዓለም ዋንጫው ከቡድኑ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር አለመግባባት ውስጥ ገብተው እንደነበርም ይነገራል።

በተለይም ቡድኑ ባደረጋቸው የመጨረሻ ጨዋታዎች ሮናልዶን ተጠባባቂ ወንበር ላይ እንዲቀመጥ ማድረጋቸውም የሚታወስ ነው። ያደረጉበትን ውሳኔ የፖርቹጋል እግር ኳስ ማህበር ይሁንታ ሰጥቶታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.