Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ከተዋቀረ በኋላ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ብቻ 150 ሚሊየን ብር ተገኝቷል- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ከተዋቀረ በኋላ ባሉት አምስት ቀናት ውስጥ ብቻ ከሀገር ውስጥ 150 ሚሊየን ብር መገኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት “ብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ከተዋቀረ በኋላ ባሉት አምስት ቀናት ውስጥ ብቻ የኢትዮጵያን ሕዝብ ደግነት ለመመልከት ችለናል” ብለዋል።

እስከ አሁን ድረስ በዓይነት የተለገሱትን የሕክምና መገልገያ አቅርቦቶች ሳይጨምር፤ ከሀገር ውስጥ 150 ሚሊየን ብር ተዋጥቷልም ብመዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ከ241 ሺህ የሚበልጡ ሰዎች ደግሞ ከሀገር ውስጥ በኢትዮቴሌኮም አማካኝነት 2.7 ሚሊዮን ብር ማዋጣታቸውንም አስታውቅዋል።

“በልዩ ልዩ ሁኔታ ውስጥ ያለን ኢትዮጵያውያን በመከራ ወቅት በአንድነት በመቆም እንደምናሸንፍ የገለጽንበት፣ መደመርን በግልጥ ያሳየንበት አጋጣሚ ነው” ብለዋል ዶክተር ዐቢይ በመልእክታቸው።

ሁሉም የቀረበለትን ጥሪ ተቀብሎ ምላሽ በመስጠቱ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፥ “ይፋ በሆኑት የመንግሥት የድጋፍ ማሰባሰቢያ መንገዶች አማካኝነት ድጋፍ ማድረጋችሁን እንድትቀጥሉ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ አቀርባለሁ” ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.