Fana: At a Speed of Life!

በሕዳር ወር ከ32 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 7፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፈው ሕዳር ወር ከ32 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ በበጀት ዓመቱ ሕዳር ወር 30 ቢሊየን 20 ሚሊየን 180 ሺህ ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ÷ 32 ቢሊየን 785 ሚሊየን 760 ሺህ ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 109 ነጥብ 21 በመቶ ማሳካት መቻሉ ተገልጿል፡፡

አፈጻፀሙ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም የ9 ቢሊየን 380 ሚሊየን 130 ሺህ ብር ወይም የ40 ነጥብ 8 በመቶ እድገት እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

በተመሳሳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ5 ወራት ውስጥ 196 ቢሊየን 536 ሚሊየን 690 ሺህ ብር ሊሰበስብ አቅዶ 195 ቢሊየን 771 ሚሊየን 570 ሺህ ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 99 ነጥብ 61 በመቶ ማሳካት መቻሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

አፈጻጸሙ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም የ48 ቢሊየን 403 ሚሊየን 270 ሺህ ብር ብልጫ ያሳየ ሲሆን÷ ይህም የ32 ነጥብ 85 በመቶ እድገት እንዳለው ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.